Ethiopian Freight Forwarders and Shipping Agents Association

ENA – ኢትዮጵያን ከነጻ የንግድ ቀጣና የበለጠ ተጠቃሚ ለማድረግ ዘርፉን በአሰራር መደገፍ ላይ ትኩረት ተደርጓል፡፡

Article:

ኢትዮጵያን ከነጻ የንግድ ቀጣና የበለጠ ተጠቃሚ ለማድረግ ዘርፉን በአሰራር መደገፍ ላይ ትኩረት ተደርጓል፡፡

Snippet:

የዕቃ አስተላላፊዎችና መርከብ ወኪሎች ማህበር ፕሬዝዳንት ኤልሳቤት ጌታሁን ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ያቋቋመችው ነጻ የንግድ ቀጣና ውጤታማ እንዲሆን ማህበሩ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ለሁለት ሳምንት ሰልጥነው ለምርቃት የበቁት ሰልጣኞች ማህበሩ ከሚሰራቸው ስራዎች መካከል አንዱ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ነጻ የንግድ ቀጣና ከንግድ ባሻገር ቱሪዝምን ለማስፋፋት ያለው ፋይዳ ከፍ ያለ በመሆኑ የበለጠ ሊሰራበት ይገባል ብለዋል፡፡

ማህበሩ ነፃ የንግድ ቀጣና በኢትዮጵያ አዲስ እንደመሆኑ መጠን በሚያጋጥሙ ችግርችና መፍትሄዎቻቸው ላይ በጥናት ለይቶ የመፍትሄ አካል ለመሆን እየተንቀሳቀሰ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ በቅርቡም በድሬዳዋ 100 ለሚሆኑ ባለሙያዎች በነጻ ንግድ ቀጣና ዙሪያ የአቅም ግንባታ ሥልጠና ለመስጠት ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል፡፡ በቀጣይም ማህበሩ ዘርፉን ለማዘመንና ለማሳደግ የሚረዱ ተግባራትን ለማከናወን ጥናትና ምርምር ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራም አረጋግጠዋል፡፡

Link:

Share on

Facebook
Twitter
LinkedIn
Telegram
WhatsApp
Email

More Updates